መአዛኤል እና አብይናቡከደነፆር

ከኢያሱ ኤፍሬም ለንደን  ታህሳሰ 18 2014

መግቢያ

በግሌ የመፀሀፍ ቅዱስ ጥልቅ እውቀት የሌለኝ ብላቴና ነኝ፡፡ ነገር ግን በማናቸው አጋጣሚ  ቃለ ሕይወት አዳምጣልሁ ፡ አነባልሁ፡፡ በተለይ የዘመኑ ጥበብ ምስጋና ይግባው እና መፅሃፍ ቅዱስን ፡ ቁራንን ቶራን ጨምሮ በሚገርም ሁኔታ የሚያስተምሩ ብዙ መንገዶች ተፈጥረዋል ከእዚህ አንዱ በዩ ቲዩብ የሚተላለፉት ትምህርቶች ናቸው፡፡ አንዳንዴ ከመፅሃፍ ቅዱሱ የማይጠቀሱ ነገሮች በሙሁራን ይቀርባሉ፡፡ መቅደላዊት ማሪያም ኢትዮጵያዊ ነች ብለው ያስተማሩ ሙሁራኖች በእዚሁ መድረክ ነው ያገኘኋቸው፡፡ አወቅ ለሚሻ ዘመኑ በሚገርም ሁኔታ እውቀትም ድንቁርናም እንኩል የሚታፈስበት ዘመን ነው፡፡

እንደ ተረዳሁት መፅሐፋ ዳናኤል በጣም ጥልቅ እና ሚስጢራዊ መፅሃፍ ነው፡፡ ይህ መፅሐፍ ከተፃፋ ከ2600 አመታት በላይ አስቆጥሯል ቃሉም የአምላክ ቃል ነው፡፡ የዘመኑ መራቅ፣ ውስብስብነት እና ሚስጢራዊነት በቀላሉ ለዘመናዊ ወይም አሁን ላለንበት ዘመን በቀላሉ የሚተርጎም አይደልም ፡፡ የነገስታቱ ሕልም እና የዳናኤል ፍቺ እረቂቅ ትምህርት በውስጡ አለ፡፡

በሌላ በኩል ይህ መፅሐፍ ቅዱስ ዘመን ተሻጋሪ አልፋ እና ኦሜጋ  ከመሆኑም በላይ በውስጡ ያሉት መልእክቶች ከመፈሳዊ መልክቱ በላይ በምድራዊ አለም ለሚፈፀሙት ክስተቶችን በትክክለኛ መንገድ እና በጥለቀት እንድናይ ይረዳናል፡፡   አበው ሲናገሩ ነገር በምሳሌ እንዲሉ ነው እና አሁን የገጠመንን ፈተና እና መከራ በጥልቀት ለማሳያት ለመመርመር ከፈለኝ ከለመድነው አገላለፅ ትንትና እና እይታ ወጣ ብለን ጥንከር ባሉ ምሳሌዎች ማሳያቱ እና ማየቱ ጥሩ ከመሆኑም በላይ የተሻለ ግንዛቤ ያስጨብጣል  በሚል እምነት አለኝ፡፡  ስለሆነም ከቅድስ መፅሃፉ ቃል ተውሼ የዳንኤል እና የናቡከደነፆር ታሪክ ተምሳሌነት በመውስድ በአገራችን የገጠመንን ችግር ለማሳየት ወደድኩኝ፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ ብዙ ዳንኤሎች አሉ አንዷም የእህታችን ጋዜጠኛ መምህር መአዛ-ኤል ነች በአገሪቱም ናቢከዳነፆር ነግሶባታል ይህን በፅሁፌ በሂዳት አስረዳለሁ ፡፡ እዚህ ላይ በጥልቀት ማሳስብ የምወደው ነጥብ እያንዳንዱ ነገር መሳ መሳ ተመሳሳይ እንዳልሆነ ነው እነዚህ ላይ ነግሮችን ነፃ አይምሮ ይዞ ( Open minded)  መረዳት ያስፈልጋል::  መልካም ንባብ

ናቡከደነፆር

በመጀመሪያ የባቢሎን ንጉስ ስለነበረው ናቡከደነፆር 2ኛ የተወሰኑ ነገሮች እንበል ፡፡ ናቡከደነፆር  ከ605 ምዓ እንከ 562 ምዓ በባቢሎን የነገሰ ንጉስ ሲሆን ንግስናውን የወሰደው ከአባቱ  ናቦፖላሳር (Nabopolassar) ነው ፡፡ ናቡከደነፆር በወጣትነት ዘመኑ በቤተ መንግስት ያደገና በጎልማሳነቱ ጥሩ ጀነራል የነበር ነው፡፡ ናቡከደነፆር ግብፅ ውስጥ በመዋጋት ላይ በነበረነት ወቅት ሳለ ነሐሴ 10 605 ም ዓ አባቱ ስለሞተ ወደ ባቢሎን ተመልሶ ንግስናውን ተረከበ፡፡

ናቡከደነፆር 2ኛ  የሚታወቅባቸው  ብዙ ነገሮች አሉ ፡ በአዚህ አጭር ፅሁፍ ሁሉን ነገሮች መጥቀስ አይቻልም፡፡ ካሉት ነገሮች መካከል አራት ነጥቦችን በእዚህ ፅሁፍ እናያለን፡፡ እነዚህ አራት ነጥቦችን አብይን ከናቡከደነፆር ጋራ ያነፃፀርኩበት፣ ያመሳሰልኩበትን እና አብይን አብይናቡከደነፆር ያለኩበትን ምክንያቶች ያስረዳልኛል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ተከተሉኝ

ናቡከደነፆር ዙፋኑን አጠናክሮ ከያዘ ብኋላ ወዲያውኑ እንደ አባቱ በአካባቢው ያሉትን ግዛቶች ማስገበር ጀመር፡፡ በአዚህም መሰርት በመጀመያ ሲሪያን  ቀጥሎ ፓሊስቲኒያን እንዱሁም ይሁዳን አገር  እና አሽኬሎም የተባለውን ከተማ አስገበረ፡፡ በ (601/600) ናቡከደነፆር ከግብፆች ጋራ ባዳርገው ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት በጦሩ እና በግዛቱ ላይ ደረስበት ነገር  ግን 599/598 ባዳረገው መልሶ ማጥቃት ወይም ወረራ ተወስዶበት የነበረው ግዛት ጨምሮ ተጨማሪ ግዛት ከመያዙም በላይ እንደ ኢየሩሳሌም ያለቱን ከተሞችንም ማስገብር ቻለ፡፡

ናቡከደነፆር ከወታደራዊ ዘመቻው እና ግዛት ከማስፋፋቱ በተጨማሪ የሚታወቅበት ነገር ቢኖር በአስገበራቸው ግዛቶች የሚገኙ ሊሂቃንን ወደ ባቢሎን በመውሰድ በባቢሎናዊያን ሕግ ስርአት ቋንቋ ማስለጠን ነበር ለእዚህም ነው ዳናኤል፣ አናንያ፣ሚሳኤል እና አዛሪያ ከጉዲያ ከጁዲያ የተወስዱት ፡፡ ዳናኤል 1: 4 ንጉሡም ነውር የሌለባቸውንና መልከ መልካሞቹን፥ በጥበብ ሁሉ የሚያስተውሉትን እውቀትም የሞላባቸውን ብልሃተኞችና አስተዋዮች የሆኑትን፥ በንጉሡም ቤት መቆም የሚችሉትን ብላቴኖች ከእስራኤል ልጆች ከነገሥታቱና ከመሳፍንቱ ዘር ያመጣ ዘንድ የከለዳውያንንም ትምህርትና ቋንቋ ያስተምሩአቸው ዘንድ ለጃንደረቦች አለቃ ለአስፋኔዝ ነገረ

ናቡከደነፆር ከሚታውቀባቸው አንዱ ነገር  ባቢሎንን መገንባቱ ነው ፡፤  ናቡከደነፆር እንዲህ ብሏል በብርቱ ኅይሌ፣ ለገናናው ክብሬ ንጉሣዊ መኖርያ ትሆን ዘንድ ያሠራኋት ታላቂቷ ባቢሎን ይህቺ አይደለችምን?  ናቡከደነፆ በንግስናው ዘመን ከ50 ሚሊዮን በላይ ጡቦች በማሰራት ብዙ ድንቅ የሚባሉ ህንፃዋችን አስርቷል፡፡   ከዚህም ውስጥ የዓለም ጥንታዊ ድንቅ ስራዎች አንዱ ተብሎ የሚጠቀሰው The hanging gardens of Babylon ወይም ተጠልጣዩ መናፋሻ ስፍራ ወይም ብሄረፅጌ ነው

Andinet Park & Sheger Park - Kia Tour & Travel

ናቡከደነፆር ተንጠላጣዩ መናፋሻ

የአብይ መናፋሻ

ናቡከደነፆር ከሚታውቅባቸው የመፅሐፍ ቅዱሳዊ ታሪኮች መካከል አንዱ የሕልም ታሪክ ነው፡፡ ናቡከደነፆር ሕልም ቢያይም ከጭንቀቱ የተነሳ ሕልሙን ሊያስታውስ አልቻለም ፡፡ ሕልሙን የሚያውቅ እና ሊፋቱ ይችላሉ ያላቸውን በአገሩ የነበሩትን አዋቂዎች አስጠርቶ ሕልሙን  እንዲፋቱለት ትእዛዝ ሰጥ፡፡ ሕልሙን አውቀው ከፈቱለት እንደሚሽልማቸው ያ ካለሆነ ግን አይቀጡ ቅጣት እንድሚደርስባቸው ነገራቸው፡፡   ይህ ታሪክ በዳናኤል ምዓራፍ 2 ላይ ይገኛል፡፡  ንጉሱ የራሱን ህልም አያውቅም የማይታወቅ ሕልም እንዴት ይፈታል፡፡  እነዚህ አራት የናቡከደነፆር ባህሪያቶች በአብይ ዘንድ የምናገናቸው ናቸው፡

አብይናቡከደነፆር

እራሱን ሰባተኛ ንጉስ ነኝ ያለው አብይ ከናቡከደነፆር ጋራ በገቢርም ሆነ በባሕሪ የሚያመሳስላቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አብይ እንደ ናቡከደነፆር በቤተ መንግስት ያደገ ነው፡፡ አብይን ገና ጭቅላ ሆኖ ያሳድጉት የዘመኑ ንጉሶች ወያኔዎች ነበሩ፡፡ አብይንም በውትድርና አስልጥነው እንደ ናቡከደነፆር ጦረኛ አድርገውታል ፡፡ አብይ አሳዳጊው ሲሞት ( ወያኔ) ስልጣን ከወያኔ ተረክቧል፡ናቡከደነፆር ከአባቲ ስንግስናን እንደወሰድ ሁሉ አብይም ከጡት አባቱ ወያኔ ንግስናን ወርሷል ፡፡ ስለሆነም አብይናቢከደነፆር ብየዋልሁ፡፡

 በሌላ በኩል  አብይ ከናቡከደነፆር ጋራ የሚያመሳስለው የመናፋሻ ስፍራ ( የአንድነት ፓርክ)  መስራቱ ነው ይህ ደግሞ ናቡከደነፆር ከሰራው መናፋሻ ስፍራ ጋራ ይመሳሰላል፡፡ የአብይ የእንጦጦ መናፈሻ ስራ ፡ የአዲስ አባበ የማስዋብ ስራ  መስቀል አደባባይን ጨምሮ  ስንመለከት የአብይ ተግባር ናቡከደነፆር ስራ ጋራ በጣም ይመሳሰላል፡፡

በጥንቃቄ እና በጥበብ የምናየው ጉዳይ የአብይ ልክ እንደ ናቡከደነፆር የግዛት ማስፋፋት አላማው ነው ፡፡ አብይ  የኦሮሙማን ሕልም ለመፈፀም እና ለማስፈፀም ከፍተኛ እቅድ ያለው ሰው ነው፡፡ ይህ ምን ያህል ይሳከለታል ወደፊት የምናየው ጉዳይ ነው ፡፡ ነገር ግን አሁን በመሬት ላይ የምናያቸው ድርጊቶች ሁሉ የሚያመሩት ወደ አንድ አቅጣጫ ነው እሱም ታላቋን ኦሮሚያ በምስራቅ አፍሪካ የመገንባት ጉዳይ ነው፡፡ አብይ ወደ ስልጣን እንደ መጣ አንዱ ይፋ የሆነው እቅድ በምስራቅ አፍሪካ ታላቁን ኦሮምያ ( ባቢሎንን) መገንባት ነው፡፡

ዛሬ በትግራይ እና በአብይ መካከል የሚደረገው ጦርነት ሁለት አበይት አላማዎች አሉት ፡፡ አንዱ ለታላቋ ኦሮሚያ መመስረት እንቅፋት ሊሆን የሚችለውን የሰሜኑን ፖለቲካ ማዳከም ነው ፡፡ በመጀመሪያ ለዘመናት የቆየውን በስልጣን ጥያቄ እና ፉክክር ከፍተት በመጠቀም የአማራን እና የትግሬን ህብረት እና አንድነት ፈፅሞ ማጥፋት ሲሆን በእዚሁ ጉዞ ውስጥ አማራውን ማዳከም እና አቀመ ቢስ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ውስጥ የትግሬ ሊሂቃን እጅግ በተሳሳተ እና እብደት በሚመስል መልኩ የሄዱበት የአጥፍቶ መጥፋት መንገድ ምክንያት የእዚህ ፕሮጀክት ዋንኛ አስፋፃሞዎች ሆነ ተከስተዋል፡ ታሪክ የኋልዮሽ ስንመለከት ከዛሬ 500 አመት በፊት በቱርኮች ( ዱርቡሽ ) የታገዘውን አገር አፍራሹን ከግራኝ መሃመድ ወረራ በጋራ የመከቱት እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦች እንደነበሩ መጥቀስ እወዳለሁ፡፡ ዘመን ወደፊት ወሰደን ስናይ ደግሞ  ሻቢያ ( ኢሳያስ) የአርቦች መሳሪያ ሆኖ እነሱ የኢሳያስ መሳራያ ሆነው ኤርትራን ከማስገንጠላቸው በላይ አገሪቱን ወደብ አልባ አደረጓት ፡፤ ዛሬ በእውር አይምሮ የገቡበት ጦርነት ለኦሮሙማ ማሳሪያ ሆነው እንዲያገለግሉ አድርጓቸዋል፡፡ አብይም እድሉን በአግባቡ እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡

የአብይ እና የኦሮሙማ አላማ አማራን በመከፋፈል፣ ደካማ እና ሽባ ማድረግ ነው፡፡  ይህም አማራ በጋራ እንዳይቆም በአደረግ ለምትመሰረተዋ ታላቋ ኦሮሚያ እንቅፋት እንዳይሆን ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህ ናቡከደነፆር ለሁለተኛ ጊዜ ጁዳያን ወሮ ከያዘበት ዘዴ ጋራ ተመሳሳይ ነው፡፡ Nebuchadnezzar’s strategic planning appeared in his attack on the Arab tribes of north-western Arabia, in preparation for the occupation of Judah ይህን በቅርቡ በመዋቅር የተዋቀረ ኮሚሽን ተቋቁሙለት በጥናት እና በሰነድ ተደግፎ በሚወጣው አገረ መንግስት ( Nation Building)  ምስረታ የሚገለፅ ይሆናል፡፡   ይህ ባሕሪው እና ድርጊቱ አብይን ከናቡከደነፆር ጋራ በጣም ያመሳስለዋል፡፡ አብይ ኢትዮጵያን ሳይሆን የራሱን ባቢሎንን እየገነባ ነው፡፡

ከናቡከደነፆር እየሩሳሌምን ከአስገበረ በኋላ ያደረገው እንድን ነገር ቢኖር በጁዲያ ውስጥ ያሉትን ብሩህ ሰዎች ወደ ባቢሎን ማጋዝ እና በባቢሎናዊያን ጥበብ እና እውቀት ታንፀው የእሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ ማድረግ ነው ፡፡ አብይም እንደ ናቡከደነፆር በመጀመሪያ ያደረገው በአስገበረው ምድር የሚገኙትን አዋቂዎችን መሰብሰብ እና የእሱ አገላጋይ ማድረግ ነው ፡፡ የጉዳዩ ገጠመኝነት የሚያስገርም እና የሚያስደነግጥ ቢሆንም አብይም ከወሰዳቸው ሰዎች ውስጥ ዲያቆን ዳናኤል ክብረትን እንዱ ሲሆን ናቡከደነፆር ከወሰዳቸው ሰዎች መካከል አንዱ ዳናኤልን ነው ( እንዲህ አይነት ነገር ሲያጋጥም ፈረጆች  spooky ይላሉ)፡;፡ ነገሩን ይበልጥ አስዳንጋጭ የሚያደርገው ሁለቱም ዳንኤሎች እጅግ መንፋሳዊ መሆናቸው ነው ፡፡  ዛሬ ዳንኤል ክብረት አብይ ያያቸውንም ሆነ ያላያቸውን ሕልሞች  ፈቺ ነው፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ አብይ መከላከያ ወደ መቀሌ አይገባም ብሎ ትእዛዝ ሲስጥ እና አብይ በችኮላ የምናዳረገው በነገር የለም ሲለን የአብይናቡከደነፆርን ህልም/ቅዘት የፈታልን ግን ወንድማችን ዲያቆን ዳናኤል ክብረት ነው የሕልሙም ፍቺ እንደሚከተለው ነው፡፡  የዛሬው ሌሊት ስም "መጥረቢያውን መሳል" ይባላል። ብልጥ ሰው ዝም ብሎ ሲጠርብ አይከርምም። ጠረብ ጠረብ ያደርግና፣ ፋታ ወስዶ፣ ለተሻለ ውጤት መጥረቢያውን ይስላል። ሞኝ እንጨቶች ደግሞ መጠረብ የቀረ ይመስላቸዋል። እየተሳለ ነው።”  ሌሊት የሚለው ሕልም ለሚለው መተኪያ ይሆን?

ሌላኛው አብይናቡከደነፆር ሕልም አላሚውም አያውቀውም ግን ፈቺው ዳናኤል ክብረት እንዲህ ይፈታልናል ፡፡ ሌላኛው የዛሬው ቀን ስም "ትዕቢተኛ ሽሮ" ይባላል። የሚፈላ ሽሮ ሲጠግብ፣ ድስቱን ካልሰበርኩ ክዳኑን ካልገለበጥኩ ይላል። ሀገሩን ሁሉ ተፈናጥሮ ለማቃጠል አጉራ ጠናኝ ይላል። ውኃ ጠብ ሲልበት ግን.. ትዕቢተኛ ሽሮ ያለበት አባዜ  ባናቱ ላይ ውኃ በገባበት ጊዜ፡፡ በነገራችን ላይ አብይናቡከደነፆር የሰበስባቸው የእየሩሳሌም ስዎች መካከል አንዱ ( እረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ፡ እና መስሎቹ ናቸው) ይህን ቃል አስታውሱ በጥበብ ሁሉ የሚያስተውሉትን እውቀትም የሞላባቸውን ብልሃተኞችና አስተዋዮች የሆኑትን፥\በንጉሡም ቤት መቆም የሚችሉትን ብላቴኖች መርጦ እንደወሰደ ቃሉ ይናገራል፡፡  

በመፀሐፈ ዳንኤል በምዕራፍ 4 11-17 ላይ  የተጠቀሰ ሕልም ዛፉም ትልቅ ሆነ፥ በረታም፥ ቁመቱም እስከ ሰማይ ደረሰ፥ መልኩም እስከ ምድር ሁሉ ዳርቻ ድረስ ታየ።”  የሚለው ቃል አብይናቡከደነፆር ይድረስ አይድረስ እንደሆነ የሚታወቅ ነገር ለአሁኑ የለም፡፡ ነገር ግን በአዚህም አለ በእዛ ተመሳሳይ ሁኔታ ይከሰታል የሚል እምነት አለኝ ፡፡ የዳናኤል ክብረት እጣፋንታ ምን እንደሚሆን ለማውቅም አይቻልም ፡፡ በመጪው ንጉስ ለአንበሶች ይሰጥ አይሰጥ ወደፊት የሚታይ ነው፡፡ ነገር ግን አብይናቡከደነፆር ዘመን ለአንበሶች የተጣላች ነፍ አለች እሷንም መአዛኤል ብያታለሁ፡፡

መአዛኤል

በባቢሎን ከነገሱት ነገስታት መካለል አንዱ ዳርዮስ ነው ፡፡ ይህም መንግስት ከሚታወቅባቸን ነገሮች አንዱ ነብዩ ዳናኤልን በአንበሶች ማደሪያ መወርወሩ ነው፡፡ የንጉሱ ባለሟሎች ዳርዮስ ዘንድ ቀርበው አንተ የምድር አምላክ ነህ በግዛትህ ያለ ሁሉ ለአንተ ማምለክ እና  መስገድ አለባቸው ብለው ነገሩት፡፡ ይህንን ያላደረገ በሕጉ መሰረት በአንበሳ ማዳሪያ እንዲወረወር ብለውን አዋጅ አስነገሩ፡፡ ዳናኤል 66-9፡፡ ይህ እንግዲብ የባቢሎን የኮማንድ ፖስት አዋጅ መሆኑ ነው፡፡ ልብ በሉ

ዛሬም አማካሪዎቹ በመከሩት መሰረት በአብይዳርዩስ  እኔን ብቻ ስሙ አምልኩ የሚል ሕግ አሳውጆል፡፡ ይህንን ሕግ የጣሰ ያለምንም ጥያቄ ዘብጥያ ይጣላል፡፡ እነሆ የተላላፈውን ሕግን ጥሰሻል በሚለ ከስ ጋዜጠኛ መአዛ ( ኤል) በአውሬዎች ማዳሪያ ተወርውራለች፡፡ ልክ የዳርዮስ አገልጋዮች የነበሩ እና የፀሎቱ ሕግ እንዲወጣ ያደረጉ ስዎች አይነት ዛሬ በአብይ ዙሪያ ከበው የሚዲያ እና የተለያዩ ሕጎችን በማውጣት እውነተኛ እና ታታሪ ኢትዮጵያኖችን ለእስር እየዳረጉ ይገኛሉ፡፡  መአዛኤልም እንደ ነብዩ ዳናኤል በእውነቷ እና በእምነቷ ከአራዊቶች መንጋጋ ተርፋ ከጠጣለችበት ዋሻ ያለምንም ጉዳት እንደምትወጣ ጥርጥር የለኝም፡፡ ነገር ግን አብይዳርዮስ የመአዛኤል አምላክን ( እውነትን) ተቀብሎ በግዛቱ ሁሉ እውነት እንዲስበክ ያድርግ አያድርግ የሚታውቅ ነገር የለም፤፡ ግን መገመት የሚቻለው ልክ እንደ ዳርዮስ አገልጋዮች የአብይ አገልጋዮችም ጊዚያቸውን ጠብቀው በዋሻ መወርወራቸው አይቀሬ ነው ፡፡

ማሳረጊያ

በእዚህ ፅሁፍ ለማስተላለፍ የተፈለገው ቁም ነገር መሰረት ያደረገው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ክርስቲያኑ ሕብረተስብ በእጁ ባለው ቅዱስ መፅሃፍ ነው፡፡  ይህ አቀራረብ ለየት እንደሚል አውቃለሁ ፡፡ ነገር ግን አንባቢያን ዛሬ በአገራቸው  እና በሕልውናቸው ላይ የሚፈፀመውን እንዲያይ እንዲያስተውሉ እና እንዲተርጉሙ ይረዳል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በእርግጥ ነው ነገሮች ቃል በቃል ፡ ላይገጣጠሙ ላይተረጎሙ ይችላሉ ነገር ግን የአምላክ ቃል እንደ መስታውት የሚያሳየን እውነታ አለ፡፡ የነገስታቶች ልብ ዘመን በማይሽረው ሁኔታ ተመሳሳይነት አለው፡፡  በባቢሎኑ በናቡከደነፆር እና ዳርዮስ እንዲሁ በኦሮሙማው በአብይ መካከል 2600 አመታት ልዩነት አለ፡፡ ግን በምግባራቸው ብዙ የሚያመሳስላቸው ነገሮች አሉ፡፡ ይህ ማወቅ አብይ ምን ሊያደርግ እንደሚችል እና  ምን ሊሆን እንደሚች ጠቋሚ አቅታጫ ይስጣል ፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን ምንም አዲስ ነገር የለም ብሎናል፡፡ ዛሬም አብይናቡከደነፆር እና አብይዳርዮስ  በምድራችን ላይ አሉ፡፡ እነሱ የሚሉትም የምታምኑት አምላካችሁ ያድናችሁ ነው፡፡  ዛሬም በተለያየ መልኩ የቅዱሷ ምድር የእስራኤል ልጆች እሉ እነሱንም መአዛኤል ብለናቸውል ፡፡ የእስራኤል ልጆችን በጣኦት አምላኪዎች ተማርከው ተወስደዋል በነሱም ልሳን ወገኖቻቸውን እንዲያናግሩ ተደርገዋል፡፡ እኛም ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የምንለው ያለ ምክኛት አይደለም፡፡ ወደ ባቢሎን የተወሳዳችሁ የእስራኤል ልጆች ወደ መቅደሳችሁ ተመለሱ እንላለን፡፡ ተግባባን