የመጀመሪያውን ዓለም ዓቀፍ አማራ ጉባኤ ዓላማን በበቂ ለማሳካት በቅድመ ጉባኤው ድረገጽ ጠንካራ የሃሳብ ልውውጥ ተሳትፎ ይኑረን የመጀመሪያውን ዓለም ዓቀፍ አማራ ጉባኤ ዓላማን በበቂ ለማሳካት በቅድመ ጉባኤው ድረገጽ ጠንካራ የሃሳብ ልውውጥ ተሳትፎ ይኑረን በዚህ የመጀመሪያ ዓለም ዓቀፍ የአማራ ጉባኤ በአማራው ማህበረሰብ ላይ የተጋረጡትን የህልውና ችግሮችን ለመቅረፍ በውጭ ሃገር የሚንቀሳቀሱ የትውልደ አማራ ቡድኖች የትግል አቅጣጫን በጋራ በመቀየስ አብሮ የመስራትና የአስቸኳይ ጥሪ ምላሽ ባህልን የሚያዳብሩበት መድረክ እንደሚሆን ይታመናል ። በዚህ ጉባኤ የሚከተሉት ጉዳዮች ውይይትና የውሳኔ መግለጫ ይሰጥባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፥ ሀ፡ የአማራ ህዝብ ትግል ከየት ወዴት የግንዛቤ መሰረቶችና አስገዳጅ አሁናዊ የትግሉ የትኩረት አቅጣጫ ትንታኔ ለ አለም ዓቀፍ ትግሉን ለማጠናከር ወሳኝና አስፈላጊ መዋቅራዊ ቅድመ ሁኔታዎችና ተዛማጅ እሳቤዎች ሐ: የአማራ አለም አቀፍ ትግልን ወደ ተገቢ ፍጻሜ ለማድረስ የተቀናጀ የዓላማና የመርሃግብር ትስስር ስለመዘርጋት የጉባኤው አደረጃጀት በተወሰነ የሰዓት ሰሌዳ ውስጥ ጉባኤው በተናጋሪ ብዛት እንዳይጨናነቅ ፤ አስተያየቶች ሳይዘለሉ ጠቃሚ ሀሳብና ውሳኔዎችን በተላየየ መንገድ ለማካተት የተሰብሳቢዎችን የተሳትፎ በአራት ደረጃ ለማስቀመጥ ሞክሯል። ፩፡ ጉባኤ አድራጅ መማክርት (Presidium-7 members) የጉባኤ መማክርት አባላትን ሲይዝ፡ እነዚህ መማክርት የአማራ ተቋምና የሙያ ተወካዮች እንዲሁም የትንታኔ ጉዳይ ተጠሪዎችን በማነጋገርና በማገናዘብ ቀጣይ የጉባኤ ዝግጅትን ያደራጃሉ ። የጉባኤው መማክርት በጉባዔው ወቅት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን በአወያይነት የመምራትና ፣ በጉባዔው ስም ጋዜጣዊ መግለጫን እንዲሁም የጉባኤውን አካሄድና የማጠቃለያ ውሳኔ ሃሳቦችን በሰነድና በጉባኤው የዌብ ሳይት ላይ ያሳውቃሉ። የጉባኤው መማክርት አባላት የተግባቦት ችሎታቸው ወይም በሚያስፈልግ ሙያዊ እውቀት የላቀ ችሎታ ያላቸውና በጉባዔውን አባል ድርጅቶች ለአንድ የጉባዔው የእንቅስቃሴ ዘመን የሚወከሉና የሚያገለግሉ ይሆናል። ፪፡ የተመረጡ ተንታኝ አቅራቢዎች (11)ተንታኝ አቅራቢዎች በጉባኤው መማክርት አባላት ተመርጠውና ተደልድለው ወቅታዊ ርዕስ ላይ የጊዜ ሰሌዳ በመጠበቅ በተመደቡበት የትንታኔ ርዕስ የተቀመጠውን ሃሳብ በተደራጀ መልክ በማቅረብ ውይይትን በተገቢው ደረጃ ያመቻቻሉ። ፫፡ የአማራ አለም ዓቀፍ ጉባዔ እንደራሴዎች (AIC Deligates : 30-35 members) 1- የአማራ አለም ዓቀፍ ጉባዔ እንደራሴ የሚወከለው ከአማራ ማህበራትና የሙያ ተቋም ወይንም የበጎ አድራጎት ሥራ ጽቤት የላቀ አስተዋጽኦ ላለው ሲሆን ውክልናው የሚጸድቀው በጉባኤው መማክርት ታጭቶና አግባብ ባለው የጉባዔ ስርዓት ሲጸድቅ ብቻ ነው። ይህ ውክልና የሚሰጠው ትውልደ አማራ ከሙሉ ክብር ሃላፊነትና ግዴታ ጋር የጉባኤውን ዓላማ በባለቤትነት ለማራመድና ውጤታማ ለማድረግ ፈቃደኛ ለሆነ ግለሰብ መሆን አለበት። 2- ለአማራ አለም ዓቀፍ ጉባዔ እንደራሴነት የሚታጨው ሰው ባለፈው አርባ አመታት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአማራ ህዝብ ጥቅም ክብር ልዕልና በጎዱ ገዢ በሆኑና በነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአድርባይነት ያልተሳተፈ መሆን አለበት ። 3- በተጨማሪም ይህ የአማራ አለም ዓቀፍ ጉባዔ እንደራሴነት እውቅና በሃገር ውስጥ ወይንም በውጭ ሃይሎች ጸረ አማራ እንቅስቃሴ ልሳን ሆኖ ያልተሳተፈ እንዲሆን ያስገድዳል። 4- የእነዚህ ተወካዮች አመራርጥ ()ለቡድናዊነትና ጎጠኝነት ሥፍራ የማይሰጡ() የአማራን ትግል በተገቢው የማመዛዘን ብቃት ያላቸው ()ግለኝነት የማያጠቃቸው ()የተግባቦት ችሎታቸው ወይም በሚያስፈልግ ሙያዊ እውቀት የላቀ ችሎታ በሚሉ መስፈርት ዙርያ የጉባዔውን አባል ድርጅቶች ለአንድ የጉባዔው የእንቅስቃሴ ዘመን የሚወከሉና የሚያገለግሉ ይሆናል። ፬፡ አድማጭ ተሳታፊ(በድምጽ የማይናገሩ( 950 listening participants) ተናጋሪ ባልሆነ የአማራ ጉባኤ የአድማጭ ተሳታፊነት የተሳትፎ ደረጃ በዐማራ ተቋሞች ያሉ አባላትን ወደጉባኤው በዲጂታል መረብ በማቅረብ ለእንቅስቃሴው ደጀን አንዲሆኑ ያመቻቻል።። እነዚህ ተሳታፊዎች በአማራው ህብረተሰብ ያላቸውን ተቆርቋሪነት የመድረክ ስነስርዓትና ግለሰባዊ ምግባር በሚያስቀድም መልክ ጠቃሚ ሃሳቦችና ጥቆማዎች ወይንም ጥያቄዎችን ለዚህ ሲባል በተዘጋጀ የዲጂታል ሰሌዳ በወቅቱ ለመማክርቱ በማቅረብ ለውይይት እንዲጠቆም ካልሆነም በማጠቃለያ ሰነድን ወይንም ለቀጣይ ጉባኤ እንዲካተት ማስደረግ ይችላሉ።

Call to action behind International Amhara Congress (IAC),

by joining crucial pre-session social media conversation !

This is to formally announce following unpresented efforts by so many Amhara organizations abroad, international Amhara Congress(IAC) will hold its first assembly on the state of Amhara struggle during the last week of April 2022 The congress is expected to discuss and pass resolutions on the following.

A-The overarching objectives of Amhara struggle abroad past and present

B- The case for IAC in facilitating Amhara International struggle into a success story

C- The way forward for Amhara struggle to bring about constitutional changes The assembly participants will be organized at four level

1-The presidium seven-members counsel appointed to coordinate proceedings of IAC

2-Selected Speakers with experience and notable expertise on 11 topic to be presented

3-Amhara delegates(30-35 members ) identified by the IAC presidium based on leadership role in Amhara organization and Amhara professional circles & has not been identified as an accessory to Amhara adversaries in the past four decades

4- General Public- as a listening congress audience , may present registered questions , reservations and comments through the presidium for the proceedings Please go on line at iac. congress@net and look up on the topics & speakers selected for 1st IAC session and join us on the telegram and twitter space assigned build a pre-congress conversation .

On